በአዲስ ከተማ አጠቃላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ06/01/2017ዓ.ም የትምህርት የመክፈቻ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ አከናውኗል፤በእለቱ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብሩክ ተክለማሪያም ፤መምህራን አስተዳደር ሰራተኞች የወላጅ ተወካዮች፤ወላጆች ተገኝተዋል፡፡የእለቱን የመክፈቻ ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ እንዳልካቸው ደጀኔ እንዲሁም የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በመጨረሻም ለተማሪዎች ደብተር ዩኒፎርም እርሳስና እስኪርብቶ ተሰጥቶ ነባርና አዲስ ተማሪዎች የችቦ መለዋወጥ ስነ-ስራዓት ተከናውኗል የፕሮግራም ፍጻሜ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በጋራ ተከናውኗል፡፡