Addis Ketema General Secondary School
Home 10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር

-
|
02:35 AM - 09:35 AM

10ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የስፖርት ሊግ ውድድር የመክፈቻ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ስቴዲየም በድምቀት በዛሬው እለት ተጀመረ።


(መጋቢት 13/2017 ዓ.ም) ስፖርታዊ ውድድሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በጋራ "የትምህርት ቤቶች ስፖርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን የመክፈቻ መርሀ ግብሩ  ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆች ፣የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ስቴዲየም በድምቀት ተካሂዷል።

ስፖርታዊ ውድድሩ  በአትሌቲክስ፣በጠረጴዛ ቴኒስ፣በቼዝ፣በቅርጫት ኳስ፣በመረብ ኳስ ፣በእግር ኳስ፣በእጅ ኳስ፣በውሀ ዋና፣በባህል ስፖርቶች፣በገመድ ጉተታ እንዲሁም የፓራሌምፒክ የውድድር አይነቶች በተማሪዎች እና በመምህራን መካከል ከትምህርት ሰአት ውጭ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Copyright © All rights reserved.

Created with