Addis Ketema General Secondary School
Announcement 186 ተማሪዎችን በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ነጥብ እንዲያመጡ አስችሏል

186 ተማሪዎችን በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ነጥብ እንዲያመጡ አስችሏል

25th September, 2025

የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 186 ተማሪዎችን በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ነጥብ እንዲያመጡ አስችሏል፤በዚህ ሂደት ውስጥ በማስተማር ሂደት በቀጥታ የፊት መሪ ሆናችሁ  ምርጥ እንቁ የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራንን የዜግነት ግዴታችሁን በመወጣትና የልፋታችሁን ፍሬ ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለዚህ ተግባራችሁ እናመሰግናለን፤ ይህ ውጤት በቂ አይደለም ነገርግን በ2018ዓ.ም በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተረከብናቸውን የማህበረሰቡን ልጆች የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያነሳሳን ነው፤ውድ ተማሪዎች በት/ቤታችን ለመማር የተቀበልናችሁም ሆናችሁ ከዚህ አንጋፋ ተቋም  በውጤት ያጠናቀቃችሁ፤የሪሜዲያል መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ የኮሌጅ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ በአጠቃላይ በ2017ዓ.ም በተቋማችን የተማራችሁ በ2018ዓ.ም ለመማር ተቋሙን የተቀላቀላችሁ  ሁሉ በመጣው ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with