Addis Ketema General Secondary School
Announcement 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ

11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ

24th April, 2026

"በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር!" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 11ኛዉን ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ከሚያዚያ 16-18/2018  . ድረስ "በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር!" በሚል መሪ ሀሳብ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች የትምህርት አመራሮች የትምህርት ባለድርሻ አካላት የትምህርት ባለሙያዎች መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በአራዳ ፓርክ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡
የሶስት ቀናት ቆይታ የሚያደርገው 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የመክፈቻ መርሀ ግብሩም በዛሬው እለት በድምቀት የተካሄደ ሲሆን እውቀት ችግሮችን ደጋግሞ ማውራት ሳይሆን ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅ እና ችግርን ወደ ድል መቀየር  ስለሆነ፣ ከተማችንን የሳይንስና ፈጠራ ማዕከል ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎች በመስራት ውጤቱንም በተጨባጭ ማየት የተጀመረበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ይህ ውጤታማ ጅምሮ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነትታውን በአግባቡ መወጣት ይኖርባቸዋል።
ዛሬ የፈጠራ ስራችሁን ያቀረባችሁ ተማሪዎችና መምህራን፣ የፈጠራ ስራችሁ  አድጎና በልጽጎ ለከተማችን፣ ለሀገራችን ብሎም ለዓለም የሚተርፍ በረከት ሊሆን እንደሚችል ትልቅ ተስፋ ሰንቀናል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with