Addis Ketema General Secondary School
Home በኢ-ስኩል አጠቃቀም እና LAN SCHOOL ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ

በኢ-ስኩል አጠቃቀም እና LAN SCHOOL ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ ተደረገ

21st May, 2025

(ግንቦት 12/2017 .) በልምድ ልዉዉጡ  መድረክ  ሁሉም የመንግስት ቅድመ 1 እና መካከለኛ ደረጃ /ቤት 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ ሁሉም የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘሮች፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት /ቤት አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎች እና ባለሞያዎች፤የተሳተፉ ሲሆን   በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ልምድ ልዉዉጥ ተደርጓል፡፡
አዲስ ከተማ አጠቃላይ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሃሌሉያ  ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና  መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  በአጠቃላይ -ስኩል  ስራዎችን እና  ስኩል ፖርታል  አጠቃቀማቸዉን ያካፈሉ ሲሆን   በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት    በፀጋው አየለ እና በሃሌሉያ ቅድመ አንደኛ ፣አንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤት  በኩል አስቻለዉ ዘገዬ   ስራቸዉን አቅርበዋል፡፡ በየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  LAN SCHOOL    አጠቃቀም ዙሪያ  የአይሲቲ ላቦች ላይ ምልከታ በማድረግ   ልምድ ልዉዉጥ የተደረገ ሲሆን  የትምህርት ቤቱ የአይሲቲ ባለሙያዎች  የላቦችን አደረጃጃት እና LAN SCHOOL ጠቀሜታ ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም  የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ዋና /መምህር አቶ እንዳልካቸዉ ደጀኔ፣ የሃሌሉያ ቅድመ እንኛ፣አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ /ቤት ዋና / መምህር  አቶ ግርማ ሽታ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ //ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ  በጋራ በልምድ ልዉዉጡ ተሳታፊዎች  ለተነሱ  ሃሳቦች ማጠቃለያ  የሰጡ ሲሆን  ተሳታፊዎችም የወሰዱትን ልምዶች እንደሚያሰፉ በመግባባት የዕለቱ ልምድ ልዉዉጥ ተጠናቋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with