እንኳን ደስ አላችሁ!!
አዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2016ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ተማሪ ህይወት እንዳለ 539/600 ተማሪ ሱሀይብ ነስሬ 525/600 ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በ27/01/2017ዓ.ም የታብሌት እና የምስጋና የምስክር ወረቀት እውቅናና እና ሽልማት አግኝተዋል፤በዚህ ሽልማት ውስጥ ባትካተቱም በርካታ ውጤታማ ተማሪዎቻችን በአርአያነት የምትጠቀሱ እንዳላችሁ አንዘነጋም እናንተም ባላችሁበት ምስጋናችን ይድረሳችሁ፤የአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2016ዓ.ም 148 ተማሪዎችን በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ በማድረግ ውጤታማ ተግባር አከናውኗል፤ለዚህ ውጤት መምጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራችሁ እንቁ መምህራንና የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ይህ የአርአያነት ተግባራችን በ2017ዓ.ም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡