አዲስ ከተማ አጠቃላይ
2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከተማሪዎች ወላጆች ጋር በሚከተሉት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡
1.የ2016ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017ዓ፣ም እቅድ በተመለከተ
2.የተማሪዎች የዲስፕሊን መመረያን ማሳወቅ በተመለከተ
3.የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርት ውጤት ማሻሻል በተመለከተ
4.አራትዮሽ ፊርማ በተመለከተ
5.የወተመህ ኮሚቴ መልሶ ማደራጀት
በአጠቃላይ ከ1 እስከ
5 ያሉትን አጀንዳዎች የት/ቤቱን አጠቃላይ መነሻ ሰነድ በዝርዝር በማቅረብ ጥንካሬና ክፍተቶችን ማሳየት የተቻለ ሲሆን በቀጣይ መሰራት ያለባቸውም ነጥቦች በዝርዝር ተገልፀው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማሻሻል ወላጆች ከት/ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፤ት/ቤቱም የተረከባቸውን ተማሪዎች በእውቀት በክህሎትና በአመለካከት በመቅረጽ ውጤታማ ሀገር ተረካቢ ዜጎች እንዲሆኑ ለመስራት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን ለወላጆች ቃል በመግባት የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡