Addis Ketema General Secondary School
Home የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

10th May, 2025

2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂ(12 ክፍልፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል፡፡
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?
➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች  ሰኔ 23  ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 /
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ 1 ዙር ተፈታኞች ሰኔ 23  ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 /
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ 2 ዙር ተፈታኞች ሰኔ 26  ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 /
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?
➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች  ሐምሌ 1  ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 /
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ 1 ዙር ተፈታኞች  ሐምሌ 1  ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 /
➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ 2 ዙር ተፈታኞች  ሐምሌ 4  ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 /
የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 / እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 / ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡
 በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ በሚከተለው ሠንጠረዥ ተገልጿል፡፡ 
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ እናበረታታለን፡፡ 
 በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ዝርዝሩ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡ 
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
 

.

Copyright © All rights reserved.

Created with