በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ስር ባሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ቀናት መቁጠሪያ ቀናት የትምህርት ካላንደር
ከ ሀምሌ 01 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ይካሄዳል።
ከነሀሴ 2 4 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ይደረጋል፡፡
ከነሀሴ 26 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም የክፍለ ከተማ የትምህርት ጉባኤ ይደረጋል፡፡
ከነሐሴ 28 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ምመምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ጉባኤ ይደረጋል፡፡
መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለተማሪዎች ህግና ደንብና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ገለፃ በክፍል ኃላፊ መምህራን ይሰጣል፡፡
ከመስከረም 3 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በልዩ ልዩ ትምህርት ቤት ዕቅድና ተያያዥ ጉዳይ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ (day one) ይጀምራል፡፡
ከህዳር 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል፡፡
ከጥር 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ/ም የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ነው።
ከጥር 25 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ፈተና ውጤት የሚያርሙበትና ውጤት ማጠናቀሪያ ሳምንት
ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም መምህራን የተማሪዎች ውጤት የሚያሳውቁበት ቀን ይሆናል፡፡
የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ/ም የሁለተኛ ሴሚስተር መደበኛ ትምህርት ይጀምራል።
የካቲት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአንደኛ ወሰነ ትምህርት በተማሪ ውጤት ዙሪያ ከወላጅ ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡
ከሚያዝያ 12 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት አጋማሽ ፈተና ይሰጣል፡፡
ከግንቦት 24 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በበይነ መረብ (online) ይሰጣል፡፡
ከሰኔ15 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ይሰጣል፡፡
ከሰኔ 22 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና የሚታረምበትና ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ጊዜ ይሆናል፡፡
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 15 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የ2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ታሳቢ ሆኖ በትምህርት ምዘናዎችና አገልግሎት ሊሻሻል ይችላል፡፡
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የስራና ተግባር ትምህርት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት ምርቃት ቀን ይሆናል፡፡
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የውጤት መግለጫ ካርድ በመስጠት የዓመቱ ትምህርት ይጠናቀቃል፡፡